Home > Forums > Tools > HiOS > ስፖርት በኢትዮጵያ

ስፖርት በኢትዮጵያ

HiOS  |  2016-2-19 04:50 3716

ስፖርት በኢትዮጵያ ብዙ ተከታዮችና ወዳጆች አሉት፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ማህበርን ከመሰረቱት ቀዳሚ አገራት ዉስጥ ኢትዮጵያ በዋነኛነት ትጠቀሳለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ የአፍሪካን ዋንጫ ሶስቴ የማዘጋጀት እድል አግኝታለች፡፡ ከተሳተፈችባቸዉ ዉድድሮች ዉስጥም እንድ ጊዜ ዋንጫዉን ማንሳት ችላለች፡፡ ኢትዮጵያ በሀገሯ ላይ ጨዋታ ሲኖራት በስታዲየም ዉስጥ ቦታ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነዉ፡፡ ስታዲየሙ በጠቅላላ በኢትዮጵያ ባንዲራ ይደምቃል፡፡ ተመልካቾች ፊታቸዉን እና የተወሰነ የሰዉነት ክፍላቸዉን በኢትዮጵያ ባንዲራ ቀለማት ይቀባሉ፡፡ ስታዲየም ዉስጥ ልዩ እና አስደሳች ድባብ ይኖራል፡፡ ከተመልካቹ አዝናኝ እና አስቂኝ የሆኑ ጭፈራዎች እና መዝሙሮች ይደመጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ እግር ኳስ እና ስፖርት ታሪክ ዉስጥ የማይረሳ ሚና ከተጫወቱት መካከል አቶ ይድነቃቸዉ ተሰማ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ አቶ ይድነቃቸዉ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይገደቡ በአፍሪካም ጭምር የስፖርት አባት ለመባል በቅተዋል፡፡ አቶ ይድነቃቸዉ ስፖርት በአፍሪካ ባጠቃላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ እነዲዘወተር እና ተወዳጅነት እነዲኖረዉ የለተለየ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሰዉ ናቸዉ፡፡ አቶ ይድነቃቸዉ ለስፖርት እድገት እና መስፋፋት ላበረከቱት ያልተቆጠበ ሙያዊ ድጋፍ እና ስራ ከኢትዮጵያ መንግሰት እና ከተለያዩ የዉጪ ድርጅቶች እና መንግስታት ልዩ ልዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በተለይ በአለም አቀፍ ደረጃ የምትታወቀዉ በረጅም ርቀት የአትሌቲክስ ዉድድሮች በምታስመዘግበዉ ድሎች ነዉ፡፡ ቀሪዉ አለም የኢትዮጵያን ረጅም ርቀት ሯጮች ስሞችን በደምብ ያዉቃቸዋል፡፡ አበበ ቢቂላ፣ ማሞ ወልዴ፣ ምሩጽ ይፍጠር፣ ሀይሌ ገብረስላሴ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ጥሩነሽ ዲባባ እንዲሁም እዚህ ጋር በስም ያልተጠቀሱ ሌሎች ጀግና አትሌቶች በአለም አቀፍ ደረጃ በተደጋጋሚ የኢትዮጵያን ስም የሚያስጠሩ አኩሪ ድሎችን አስመዝግበዋል፡፡ አበበ ቢቂላ በ1960 (እ.ኤ.አ) በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ በመሮጥ ያስመዘገበዉ አንጸባራቂ የማራቶን ድል መቼም ቢሆን የማይረሳ ነዉ፡፡ አበበ ቢቂላ ያስመዘገበዉ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካን በመወከል በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ በጥቁር አትሌት የተገኝ የወርቅ ሜዳሊያ በመሆን በታሪክ ሠፈሯል፡፡ በአሁኑ ወቅት ቴክኖ ሞባይል በአገሪቱ የስፖርት እንቅስቃሴ ላይ በጉልህ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
  • Like(0)
  • Share
You need to log in before reply Log In | Register

Haleluya 4 #

our amazing world recorders should also captured by Camon C8!!!!
2016-2-23 05:01 Like(0)

Haleluya 3 #

This amazing sport culture can be captured by C8 TECNO mobile!!
2016-2-23 04:23 Like(0)

Yohannes 2 #

ክብር ለ አቶ ይድነቃቸዉ እና ለ ጀግኖች አትሌቶቻችን!!!! ሁልጊዜም እንኮራባችኋለን!!
2016-2-22 04:20 Like(0)

Kalkidan Melese

Iron

Follow Send PM

    © 2023 TECNO Mobile